በሞባይል እና ፒሲ ላይ ከ200,000 በላይ ጨዋታዎችን የያዘ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ካታሎግ ያስሱ እና ለእርስዎ ትክክል የሆነውን ጨዋታ ያግኙ
ለጨዋታ ግዢዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን Google Play Points1 ያግኙ እና እንደ አንድ የነጥቦች አባል ለሚመለከተው የተወሰኑ ጥቅሞችን ያግኙ
የእርስዎ ተወዳጅ ጨዋታዎች እና የራስዎ የጨዋታ ስኬቶች ዝማኔዎች ሁሉ በአንድ ምቹ የእርስዎ ትር2 ላይ ይገኛሉ
ለቅናሾች እና ለውስጠ-ጨዋታ ንጥሎች የሚጠቀሟቸውን ነጥቦች እና ሽልማቶች ማግኘት የሚችሉበት የGoogle Play የሽልማቶች ፕሮግራም በሆነው በGoogle Play Points የቀጣይ ደረጃ ሽልማቶችን ይክፈቱ። ብዙ Play Points ባገኙ ቁጥር ብዙ የማይበገሩ ሽልማቶችን፣ ጥቅሞችን እና ገንዘብ-የማይገዛቸው ተሞክሮዎችን ይከፍታሉ። አሁን ይቀላቀሉ 1።
የእርስዎ ትር ወሳኙ ነገር የተጫዋች መገለጫዎ ነው። በሞባይል ላይ የመገለጫ አዶውን ጠቅ በማድረግ በማንኛውም ጊዜ ከእርስዎ ትር ወደ የተጫዋች መገለጫ በቀላሉ ማሸጋገር ይችላሉ። አንድ መገለጫን በመላ ሞባይል እና ፒሲ ላይ በመጠቀም የእርስዎን ስታቲስቲክስ፣ ተከታታዮች፣ ግስጋሴዎች እና ስኬቶች በመላ ጨዋታዎችዎ ውስጥ በቀላሉ መከታተል ይችላሉ። እያንዳንዱ ስኬት፣ እያንዳንዱ ድል - ሁሉም ለማክበር እዚህ ነው።
Gemini Live ያለው የPlay Games ረዳት ከጨዋታዎ ሳይወጡ ወደ ቀላል የእርስዎ ስታቲስቲክስ፣ ስኬቶች እና ጠቃሚ ምክሮች መዳረሻን የሚሰጥዎት አዲስ የጨዋታ አጋር ነው። እንዲሁም እርስዎ በሚጫወቱበት ጊዜ የእውነተኛ ጊዜ የውይይት መመሪያን ከGemini Live ማግኘት ይችላሉ። ረዳት ከGoogle Play የወረዱ ጨዋታዎችን ሲጫወቱ ብቻ ይገኛል እና በቅርቡ ወደ ሞባይል ይመጣል።
ከGoogle በሚገኝ ደኅንነት እና ጥበቃ በመላ ሞባይል እና ፒሲ ላይ በልበ ሙሉነት ይጫወቱ። Google Play የእርስዎ ውሂብ እና መሣሪያዎች ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ለማገዝ እኛ በምናቀርበው እያንዳንዱ ጨዋታ ላይ ከ10,000 በላይ የደኅንነት ፍተሻዎችን ያሄዳል።