ይህ ይዘት በማህደር ከተቀመጠው የግላዊነት መመሪያችን ስሪት የመጣ ነው። የአሁኑ የግላዊነት መመሪያችንን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።

«በጣም ጠቃሚ ሆነው የሚያገኟቸው ማስታወቂያዎች»

ምሳሌዎች

  • ለምሳሌ፣ ስለጓሮ አትክልት ያሉ ድር ጣቢያዎችን እና ጦማሮችን በተደጋጋሚነት የሚጎበኙ ከሆኑ ድሩን ሲያስሱ ከጓሮ አትክልት ጋር የሚዛመዱ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። እና YouTube ላይ ስለመጋገር ያሉ ቪዲዮዎችን ከተመለከቱ ከመጋገር ጋር የሚዛመዱ ተጨማሪ ማስታወቂያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። ተጨማሪ ይወቁ።
  • ግምታዊ አካባቢዎን ለመወሰን የአሁኑ የአይፒ አድራሻዎን ልንጠቀም እንችላለን፣ ስለዚህ «ፒዛ» ብለው ከፈለጉ አቅራቢያ ስላለ የፒዛ መላኪያ አገልግሎት ማስታወቂያዎችን ልናቀርብልዎ፣ ወይም ደግሞ «ሲኒማ» ብለው ከፈለጉ አጠገብ ባለው ሲኒማ ውስጥ ያሉ የማሳያ ሰዓቶችን ልናሳይዎ እንችላለን። ተጨማሪ ይወቁ።
  • ስርዓቶቻችን ይበልጥ ተገቢ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንደ የGmail ኢሜይሎች ያሉ በአገልግሎታችን ውስጥ ያሉ ይዘቶችን በራስ-ሰር ሊቃኙ ይችላሉ። ስለዚህ ለምሳሌ በቅርቡ ስለፎቶግራፊ ወይም ካሜራዎች ብዙ መልዕክቶች ከደረሰዎት በአንድ አካባቢያዊ የካሜራ መደብር ውስጥ ስላለ ቅናሽ ማወቅ ሊፈልጉ ይችሉ ይሆናል። በሌላው በኩል ደግሞ እነዚህን መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት ብለው ሪፖርት ካደረጓቸው ያንን ቅናሽ ማየት የማይፈልጉ ሳይሆኑ አይቀሩም። ይህ አይነት የራስ-ሰር ሂደት ብዙ የኢሜይል አገልግሎቶች እንደ የአይፈለጌ መልዕክት ማጣሪያ እና ፊደል ማረሚያ ያሉ ባህሪያትን የሚያቀርቡበት መንገድ ነው። በGmail ውስጥ ያለ የማስታወቂያ ማነጣጠር ሙሉ ለሙሉ በራስ-ሰር የሚሰራ ነው፣ እና ማስታወቂያዎችን ወይም ተዛመጅ መረጃን ለእርስዎ ለማሳየት ማንም የሰው ፍጡር ኢሜይልዎን ወይም የGoogle መለያ መረጃዎን ማንበብ አይችልም። በGmail ውስጥ ስላሉ ማስታወቂያዎች እዚህ ተጨማሪ ይወቁ።
Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ