አውቶሪ በአንድ ጊዜ በአንድ የመንገድ እይታ ምስል በመላው ፊንላንድ የመንገድ ጥገና ላይ እንዴት ከፍተኛ ለውጥ እንዳመጣ።

የመንገድ ወለሎች ጥራት፣ ጊዜ ያለፈባቸው ምልክቶች እና የጨለሙ መንገዶች በመላው ዓለም ለአሽከርካሪዎች እና ማዘጋጃ ቤቶች የየቀን ትግሎች ናቸው። ሆኖም ግን አውቶሪ፣ ለመሰረተ ልማት ጥገና መፍትሄዎችን የሚገነባው የፊንላንድ የሶፍትዌር ኩባንያ በGoogle ካርታዎች የመንገድ እይታ በመንገድ ደረጃ ያለ ውሂብን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ የመሰብሰቢያ እና የመተንተኛ መንገድ አግኝቷል።

40,000 ኪሜ

ፎቶግራፍ ተነስተዋል

8 ሚሊዮን

የታተሙ ምስሎች

50 ሚሊዮን

እይታዎች

የመንገድ ውሂብ

20

ፕሮጀክቶችን መቅረጽ

ፊንላንድ ውስጥ የመንገድ ጥገና አስተዳደርን ውጤታማነት ማሻሻል

በ1988 የተመሰረተው አውቶሪ ሶፍትዌርን እንደ የአገልግሎት (ኤስኤኤኤስ) መፍትሔዎች ለፊንላንድ የመንገድ ባለስልጣናት፣ ተቋራጮች እና ሦስተኛ-ወገን አማካሪዎች ለሁኔታ አስተዳደር፣ የእርምጃ እቅድ ለማውጣት እና ለጥገና ትብብር ያቀርባል። በመላው አገር የመንገድ ሁኔታዎችን መከታተል ብዙ ጊዜን ይወስዳል እና ብዙ ወጪን ያስከትላል፣ ነገር ግን ሌሎች ኩባንያዎች ወጪዎችን ሲያዩ አውቶሪ በልዩ እድል ላይ መጠቀም ችሎ ነበር። የራሳቸውን የመንገድ እይታ ምስሎች እና SaaS መፍትሔዎችን በመጠቀም፣ ፊንላንድ ውስጥ ለመንገድ ጥገና መሰረተ ልማት ውሂብ እና ውሳኔ አሰጣጥ የተሻለ አስተዳደር መሣሪያ ፈጥረዋል።

የፍጥነት እና የውሂብ-ማጋራት አስፈላጊነት

በተለምዶ፣ የመንገድ ባለስልጣናት በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ምን ስራ እንደሚያስፈልግ ለማወቅ በአካል ጉብኝት ማድረግ አለባቸው። ይህም ማለት በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን ማሽከርከር እና ማስታወሻዎችን ለመውሰድ ለቁጥር የበዙ ቦታዎች ላይ ማቆም ማለት ነው። ይህ ለአካባቢው መጥፎ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ወጪን የሚጠይቅ፣ በርካታ ሃብቶችን የሚመለከት እና በጣም ብዙ ጊዜን የሚወስድ ነው። ስለዚህ ወደ ዲጂታል የተቀየረ እና ይበልጥ ለአካባቢ ተስማሚ የሆነ መፍትሔ ማስፈለጉ አውቶሪን ከተለመደው ውጪ እንዲያስብ አድርጎታል። እና የመንገድ እይታ ወደ አዕምሮው የመጣ የመጀመሪያው በመንገድ ደረጃ ያለ የምስላዊ ዕይታ መፍትሔ ነበር።

 

ከመንገድ ጥገና ጋር አብሮ መጓዝ እጅግ ብዙ ቁጥር ያለውን ውሂብ ከበርካታ የተለያዩ ወገኖች ጋር በተደጋጋሚ ማጋራትን ይጠይቃል። የመንገድ ዕይታ በተጠቃሚዎች መካከል መረጃ ማጋራትን ቀላል ለማድረግ አስፈላጊው ሁሉ መሣሪያዎች አለው - ዘመናዊ ስልክ ላለው ለሁሉም ሰው ይገኛል እናም ማንኛውንም መግቢያዎች ወይም የሶፍትዌር ጭነቶች አይፈልግም። እናም ምንም እንኳን የመንገድ ዕይታ በፊትም ለመንገድ ጥገና ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ቢሆንም ውሂቡን ወቅታዊ አድርጎ ማቆየት ትልቁ ተግዳሮቱ ነበር። የመንገድ ዕይታን ከእኛ የመንገድ ጥገና ሶፍትዌር ጋር በማዋሃድ ያንን ችግር ለመጠገን መልካም አጋጣሚ አይተናል።

-

አሪ ኢሞነን፣ አውቶሪ ላይ የዲጂታላይዜሽን ኮንሰልቲንግ ክፍል ዋና አስተዳዳሪ

 

Google የመንገድ እይታ አውቶሪ የፊንላንድ መንገዶችን ካርታ ሰራ

ለየመንገድ ደህንነት መስመር ላይ እና ከመስመር ውጪን ማዋሃድ

በ2017 መጀመሪያ ላይ አውቶሪ ምስሎቹን ለማተም የኩባንያቸውን የGoogle መለያ በመጠቀም ፊንላንድ ውስጥ ያሉ የግዛት መንገዶችን 360 ምስል ፎቶግራፍ ማንሳት እና መስቀል ጀመረ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የመንገድ ጥገና አስተዳደርን መስመር ላይ በማምጣት 40,000ኪሜ የሚሆነውን የግዛት መንገዶች ሸፍነዋል እንዲሁም 8 ሚሊዮን ምስሎችን ሰቅለዋል። የመንገድ እይታን ከSaaS መፍትሔዎቻቸው ጋር በማዋሃድ ለየመንገድ ባለስልጣናት ወቅታዊ የመንገድ እሴት መረጃን በርቀት መድረስን ቀላል እንዲሆንላቸው አድርገዋል።

ምስጋና ለአውቶሪ ምስል የመንገድ እይታ ላይ ላተማቸው ይሁንና፣ የጎደሉ የመንገድ ምልክቶች፣ የምልክቶች ወይም ጉድጓዶች ሪፖርቶች በየአውቶሪ ዳሽቦርድ በኩል ከቢሯቸው ሆነው እንዲመረምሩ ለሚመለከታቸው አካላት ሊሰቀሉ እና መለያ ሊሰጣቸው ይችላል። ብጁ ሊሆን የሚችል መፍትሔን በማቅረብ አውቶሪ እንዲሁ ተቋራጮች በአንድ ቦታ ላይ አስፈላጊውን የጥገና ስራ እንዲከታተሉ እና እንዲያቅዱ ያስችላል። የጥገና ስራው ሲጠናቀቅ የመንገድ ውሂብን ወቅታዊ አድርጎ ለማቆየት የአካባቢው አዲስ የ360 ምስሎች በሰራተኞች ይነሱና ይሰቀላሉ። ይህ ምርመራ ለማድረግ አካላዊ ጣቢያዎችን የመጎብኘት አስፈላጊነትን ቀንሷል - ይህም ጊዜን፣ ገንዘብን እና የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀቶችን ቆጥቧል።

በሁሉም ቦታ ላይ የመንገድ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት

የመንገድ እይታ አውቶሪ ፊንላንድ ውስጥ ለየመንገድ ባለስልጣናት መረጃ ማጋራትን እና ሁኔታዊ ግንዛቤን እንዲያሻሽል ፈቅዶለታል፣ ይህም በተዘዋዋሪ ወጪዎችን ለመቀነስ እና ውጤታማነትን ለመጨመር አግዟል። ይህ በዓለም አቀፍ ዙሪያ ሊያመጣ የሚያስችለውን አዎንታዊ ተጽዕኖ በመገንዘብ፣ አውቶሪ አሁን ለወደፊቱ የመንገድ ውሂብን ለመሰብሰብ እና ለማጋራት የሚያስችል መደበኛ የሆነ ሞዴል ላይ እየሰራ ነው። እንዲሁም 1,000ኪሜ የብስክሌት መሄጃ እና የእግረኛ መተላለፊያ መንገዶችን ፎቶግራፍ በማንሳት የአካባቢው ሰዎች የካርቦን ብዛታቸውን እንዲቀንሱ አግዟል። ሰዎች አሁን ወቅታዊ የሆነ ውሂብን መድረስ እና አጫጭር ርቀቶችን ይበልጥ ለተፈጥሮ ተስማሚ በሆነ መንገድ መጓዝ ይችላሉ። በተጨማሪም ፊንላንድ ውስጥ ተጨማሪ 15,000ኪሜ ለመሰብሰብ በዚህ በጋ ጉዞ ይጀምራሉ፣ ይህም በአገሩ ውስጥ ያሉትን ከሁሉም የመንግስት መንገዶች ውስጥ ግማሽ ያህሉን በየመንገድ እይታ ላይ ፎቶግራፍ በማንሳት እና በማተም ያቀራርባቸዋል።

የአውቶሪ ስኬት የመንገድ እይታን ንግዶች የተወሳሰቡ ችግሮችን ለመፍታት እየተጠቀሙባቸው ካሉበት በርካታ ልዩ የሆኑ መንገዶች ውስጥ አንዱ ምሳሌ ነው። ከየፎቶ-ካርታ መስሪያ መሣሪያ በላይ ነው እናም ለእርስዎ ንግድም ሊለኩ የማይችሉ ጥቅሞች ሊኖረው ይችላል። የራስዎን የመንገድ እይታ የስኬት ታሪክ ለመጻፍ ዝግጁ ነዎት?

የራሰዎን የመንገድ እይታ ምስል ያጋሩ