360 ምስል መቼ፣ የት እና እንዴት እንደምንሰበስብ ይመርምሩ

ከGoogle ባለብዙ ቀለም የመንገድ እይታ ስምሪት ጋር ይተዋወቁ እና የዓለምን ካርታ ለማጎልበት እንዴት 360 ምስል እንደምንሰብስብ ይወቁ።

የGoogle የመንገድ እይታ ምስል ስብስብ
የGoogle የመንገድ እይታ ምስል ስብስብ የእነማ መኪና

የፎቶግራፊ ምንጮች

የመንገድ እይታ ፎቶዎች ከሁለት ምንጮች ይመጣሉ፣ ከGoogle እና ከአስተዋጽዖ አበርካቾቻችን።

የእኛ ይዘት
ይዘት ከአስተዋጽዖ አበርካቾች

የእኛ ይዘት

በGoogle ባለቤትነት የተያዘ ይዘት ለ«የመንገድ እይታ» ወይም ለ«Google ካርታዎች» እውቅና ይሰጣል። በምስላችን ውስጥ ፊቶችን እና የሰሌዳዎች ቁጥርን በራስ-ሰር እናደበዝዛለን።

የመመሪያ ዝርዝሮች

በጆርዳን ውስጥ ከፔትራ የGoogle የመንገድ እይታ ምስል

ይዘት ከአስተዋጽዖ አበርካቾች

በተጠቃሚ-የተበረከተ ይዘት ጠቅ/መታ ሊደረግ የሚችል ስም፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመገለጫ ፎቶ ጭምር አብሮ ይከተላል።

የመመሪያ ዝርዝሮች

ለመንገድ እይታ አስተዋጽዖ ያበርክቱ

የGoogle የመንገድ እይታ ምስል ፌዴሪኮ ዲቦቶ ካርታዎች ዛንዚባር

በዚህ ወር የካርታ ስራ የት እየሰራን እንደሆነ

ተሞክሮዎን የሚያሻሽለውን እና በዙሪያዎ ያለውን ዓለም እንዲያውቁ የሚያግዝዎትን ምስል ለማቅረብ በዓለም ዙሪያ እንነዳለን እና እንጓዛለን። ቡድናችንን ሰላም ለማለት ከፈለጉ በአቅራቢያዎ ወዳለ አካባቢ እነሱ መቼ እንደሚመጡ ከታች ይመልከቱ።

ቀን ወረዳ
ቀን ወረዳ

ከእኛ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ጉዳዮች ምክንያት (የአየር ንብረት፣ የመንገድ መዘጋት፣ ወዘተ)፣ መኪናዎቻችን ላይሰሩ የሚችሉበት ወይም የተወሰነ ለውጥ ሊኖር የሚችልበት እድል ሁልጊዜ ይኖራል። በተጨማሪም ዝርዝሩ አንድን ከተማ በጠቀሰበት ቦታ፣ በመንዳት በሚደረስበት ርቀት የሚገኙ አነስተኛ ከተማዎችንም የሚያካትት ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ ይያዙ።

የዓለምን አስደናቂ ቦታዎች ለማግኘት የተዘጋጀ ስምሪት

በሁሉም ሰባት አህጉሮች አስገራሚ ቦታዎችን ጎብኝተናል እና ይበልጥ ደግሞ የሚመጣ አለ መንገድ ከመጀመራችን በፊት ትክክለኛውን ስምሪት ለማሰማራት እና ምርጡን ምስል ለመሰብሰብ መልከዓ ምድሩን፣ የአየር ንብረት ሁኔታዎችን እና የህዝብ ትፍገትን ጨምሮ በርካታ ነገሮችን ከግምት ውስጥ እናስገባለን።

የመንገድ እይታ መኪና

በጣራ ላይ የካሜራ ስርዓት ያለው የመንገድ እይታ መኪናው ምስል ለመሰብሰብ ይበልጥ ጥቅም ላይ የዋለ መሣሪያችን ነው እና በዓለም ዙሪያ ሙዝ እየበላ ያለ ፈረስን ጨምሮ ከ10 ሚሊዮን ማይል በላይ እንድንቀርጽ አግዞናል።ሙዝ እየበላ ያለ ፈረስ።
የመንገድ እይታ መኪና

ተጓዥ

ይህን ተንቀሳቃሽ የካሜራ ስርዓት እንደ የጀርባ ቦርሳ ወይም ከፒካፕ የጭነት መኪና፣ ከበረዶ ተሽከርካሪ ወይም ከሞተር ብስክሌት አናት ላይ አፈናጥጦ መጠቀም ይቻላል። በጠባብ መንገዶች ወይም እንደ ኢንካ ሲታዴል ማቹ ፒቹ ያሉ በእግር ብቻ ልንደርስባቸው የምንችላቸው ቦታዎች ውስጥ ምስል እንድንሰበስብ ያስችለናል።ማቹ ፒቹ
ተጓዥ

ለካርታዎች ነፍስ በመዝራት ላይ

ምስሉን ሰብስበን ከጨረስን በኋላ ሁሉንም ወደ ማያ ገጽዎ የማምጣት ጊዜው ነው። ቡድናችን ከመድረክ በስተጀርባ ምን እየሰራ እንደሆነ የጨረፍታ ዕይታ እነሆ።

  • ምስል መሰብሰብ

    በመጀመሪያ እየተዘዋወርን በመንዳት በመንገድ እይታ የሚታዩትን አካባቢዎች ፎቶግራፍ ማንሳት አለብን። በተቻለ መጠን ምርጥ ምስል የሚገኝበትን ጊዜና ቦታ ለመወሰን የአየር ንብረትን እና የሰው ብዛትን ጨምሮ ለበርካታ ጉዳዮች ትልቅ ትኩረት እንሰጣለን።

  • ምስሎችን ማሰለፍ

    እያንዳንዱን ምስል በካርታው ላይ ከትክክለኛ ቦታው ጋር ለማዛመድ፣ ጂፒኤስ፣ ፍጥነት እና አቅጣጫ ከሚለኩ በመኪናው ላይ የተገጠሙ መለኪያዎች የተገኙ ምልክቶችን እናጣምራለን። ይህም የመኪናውን ትክክለኛ መስመር መልሰን እንድንሰራ፣ እንዲሁም ምስሎችን እንዳስፈላጊነቱ እንድናጋድል እና እንደገና እንድናሰልፍ ያስችለናል።

  • ፎቶዎችን ወደ 360 ፎቶዎች መቀየር

    በ360 ፎቶዎች መካከል ክፍተቶችን ለማስወገድ፣ ተከታታይ ካሜራዎች መጠነኛ መደራረብ ያላቸውን ምስሎች ይወስዱና ፎቶዎቹን በአንድ ላይ «በመስፋት» አንድ ባለ 360-ዲግሪ ምስል ያደርጓቸዋል። ከዚያም «ጠርዞችን» ለመቀነስ ልዩ የምስል ማቀነባበሪያ ስልተ ቀመሮችን በመጠቀም ወጣገባነት የሌላቸው መሸጋገሪያዎችን እንፈጥራለን።

  • ለእርስዎ ትክክለኛ ምስል በማሳየት ላይ

    የመኪናው ሌዘሮች ከወለሎች ላይ የሚያንፀባርቁበት ፍጥነት አንድ ህንጻ ወይም ቁስ በምን ያህል ርቀት ላይ እንዳለ ይነግረናል እና የዓለምን 3ል ሞዴል ለመገንባት ያግዘናል። በመንገድ እይታ ውስጥ በርቀት ወደ አንድ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ይህ ሞዴል ለዚያ አካባቢ ሊያዩት የሚመጠረውን ፓኖራማ ይወስናል።

የት እንደነበርን

በካርታው ላይ ያሉት ሰማያዊ ቦታዎች የመንገድ እይታ የት እንደሚገኝ ያሳያሉ። ለበለጠ ዝርዝር ያጉሉ ወይም በGoogle ካርታዎች ላይ ያስሱ።

የበለጠ ለመረዳት