Google ላይ ያለዎት ግላዊነት

እንደ ውሂብ ምንድነው? ያለ ስለግላዊነት ለሚጠየቁ አንዳንድ ከፍተኛ ጥያቄዎች መልሶች እዚህ ያገኛሉ። እንዲሁም የበለጠ መረዳት ከፈለጉ የግላዊነት መመሪያውን ይመልከቱ።

የእርስዎ አካባቢ

ወደ ርዕስ ሂድ

በGoogle ላይ ማጋራት

ወደ ርዕስ ሂድ

ውሂብ እና ግላዊነት ማላበስ

ወደ ርዕስ ሂድ

እርስዎ ነዎት የሚቆጣጠሩት

ወደ ርዕስ ሂድ

የእርስዎ አካባቢ

Google የእኔን አካባቢ ያውቃል?

በይነመረብ በሚጠቀሙበት ጊዜ መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የት እንዳሉ በደፈናው መገመት ይችላሉ፣ ይህ ለGoogleም ተመሳሳይ ነው። በመሣሪያዎ ቅንብሮች ላይ በመመስረት Google የእርስዎን ትክክለኛ አካባቢዎን ሊያውቅ ይችላል። (የእኔ አካባቢ ምን ያህል ትክክለኛ ነው?ን ይመልከቱ)

እንደ ፍለጋ፣ ካርታዎች ወይም Google ረዳት ያለ በGoogle ላይ ሲፈልጉ ተጨማሪ አጋዥ ውጤቶችን ለእርስዎ ለመስጠት የአሁኑ አካባቢዎ ስራ ላይ ሊውል ይችላል። ለምሳሌ፣ ምግብ ቤቶችን ፈልገው ከሆነ በጣም አጋዦቹ ውጤቶች ምናልባት እርስዎ ባሉበት አቅራቢያ ያሉት ምግብ ቤቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

አካባቢዎን እንዴት ማስተዳደር እንደሚችሉ ይመልከቱ

አካባቢን እንዴት ማብራት እና ማጥፋት እችላለሁ?

በGoogle ላይ ሲፈልጉ Google ሁልጊዜ የሚፈልጉበትን አጠቃላይ አካባቢ ይገምታል። Google ልክ እንደ እርስዎ የሚጠቀሙት ከበይነመረቡ ጋር የሚገናኝ ማንኛውም መተግበሪያ ወይም ድር ጣቢያ በመሣሪያዎ የአይፒ አድራሻ ላይ ተመስርቶ አካባቢዎን ሊገምተው ይችላል። ለተጨማሪ Google እኔ ያለሁበትን እንዴት ነው የሚያውቀው? የሚለውን ይመልከቱ።

Googleን ሲጠቀሙ ትክክለኛ አካባቢዎን ለመላክ ይፈልጉ እንደሆነ ለመምረጥ፣ ለግለሰብ መተግበሪያዎች፣ ጣቢያዎች እና ለመሣሪያዎ የአካባቢ ፈቃዶችን ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ።

የእርስዎን ቤት ወይም የሥራ አድራሻ ካዋቀሩ እና Google እርስዎ ቤት ወይም ሥራ ላይ እንደሆኑ የሚገምተው ከሆነ ትክክለኛው አድራሻ ለፍለጋዎ ስራ ላይ ይውላል።

የእኔ ቦታ ምን ያህል ትክክለኛ ነው?

የእርስዎ አጠቃላይ አካባቢ

በGoogle ላይ ሲፈልጉ Google ሁልጊዜ የሚፈልጉበትን አጠቃላይ አካባቢ ይገምታል። በዚህ መንገድ Google እርስዎን የሚመለከቱ ውጤቶች ሊሰጠዎት እና እንደ ከአዲስ ከተማ በመለያ መግባት ያለ ያልተለመደ እንቅስቃሴን ለይቶ በማወቅ የእርስዎን መለያ ደህንነት እንዲጠበቅ ማድረግ ይችላል ማለት ነው።

የፍለጋዎ አጠቃላይ አካባቢ እርስዎን ለይቶ ማወቅ እንዳይችል አጠቃላይ አካባቢው ከ3 ካሬ ኪሜ ስፋት በላይ ነው እና ቢያንስ 1,000 ተጠቃሚዎች አሉት፣ በዚህም ግላዊነትዎን ለመጠበቅ ያግዛል።

የእርስዎ ትክክለኛ አካባቢ

ፈቃድዎን ከሰጡ Google ትክክለኛ አካባቢዎን ሊጠቀም ይችላል። ለምሳሌ፣ እንደ «በአቅራቢያዬ ያለ አይስክሬም» ወይም ወደ መደብር ለሚወስድ ማዞሪያዎች ላሉት የጉዝ አቅጣጫዎች ፍለጋዎች በጣም ተዛማጅ ውጤቶችን ለመመለስ Google ትክክለኛ አካባቢዎን ይፈልጋል።

ትክክለኛ አካባቢ ማለት እርስዎ በትክክል ያሉበት ቦታ ማለት ነው፣ ለምሳሌ የተለየ አድራሻ።

Google እንዴት የእኔን አካባቢ ያውቃል?

የእርስዎ አካባቢ ከተለያዩ ምንጮች የመጣ ሲሆን እርስዎ ያሉበትን ለመገመት አብረው ስራ ላይ ይውላሉ።

የመሣሪያዎ አይፒ አድራሻ

የአይፒ አድራሻዎች ከስልክ ቁጥር አካባቢ ኮዶች ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በጂዮግራፊ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ይህ ማለት google.comን ጨምሮ የሚጠቀሙት ማንኛውም መተግበሪያ ወይም ድር ጣቢያ በአይፒ አድራሻዎ ምክንያት እርስዎ ያሉበትን አጠቃላይ አካባቢ ሊገምት ይችላል ማለት ነው። የመሣሪያዎ አይፒ አድራሻ በእርስዎ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ ለእርስዎ መሣሪያ የሚመደብ ሲሆን በይነመረቡን ለመጠቀም ያስፈልጋል።

የመሣሪያዎ አካባቢ

ለGoogle መተግበሪያ ወይም ጣቢያ የመሣሪያዎን አካባቢ እንዲጠቀም ፈቃድ ከሰጡ ይህ መረጃ እርስዎ ያሉበትን ቦታ ለመረዳት እንዲያግዝ ስራ ላይ ሊውል ይችላል። ሁሉም መሣሪያዎች ማለት በሚቻል ደረጃ በስርዓተ ክወናው ውስጥ አብዛኛው ጊዜ በቅንብሮች ውስጥ የተገነቡ የአካባቢ ቅንብር አላቸው።

Google ላይ ያለዎት እንቅስቃሴ

Google በቀዳሚዎቹ የእርስዎ Google ፍለጋዎች ላይ ተመስርቶ እርስዎ ያሉበትን አጠቃላይ አካባቢ ሊገምት ይችላል። ለምሳሌ፣ አብዛኛው ጊዜ በሙምባይ ውስጥ ፒዛ የሚፈልጉ ከሆነ በሙምባይ ውስጥ ውጤቶችን የማየት ዕድል አለዎት።

የእርስዎ የተሰየሙ ቦታዎች

የእርስዎን ቤት ወይም የሥራ አድራሻ ካቀናበሩ Google እርስዎ ያሉበትን ቦታ ለመገመት ሊጠቀምባቸው ይችላል። ለምሳሌ፣ የእርስዎን ቤት አድራሻ ካቀናበሩ እና የእርስዎ አይፒ አድራሻ፣ ቀዳሚ እንቅስቃሴ ወይም ሌሎች የአካባቢ መረጃ ምንጮች እርስዎ ቤትዎ አጠገብ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ከሆነ ከዚያ የእርስዎን ቤት አካባቢ እንደ እርስዎ ያሉበትን ቦታ ግምት እንጠቀማለን።

ማነው የእኔን አካባቢ ማየት የሚችለው?

የእርስዎ ጉዳይ ነው። Google አካባቢ ማጋራትን የሚጠቀሙ ከሆነ ቅጽበታዊ አካባቢዎን በመላው የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ላይ ለጓደኛዎች እና ለቤተሰብ ማጋራት ይችላሉ።

አካባቢዎን እያጋሩ እንደሆነ ያረጋግጡ

የአካባቢ ማጋራት በነባሪነት ጠፍቷል። ቅጽበታዊ አካባቢዎን ለማጋራት ከፈለጉ ለማን እና ለምን ያህል ጊዜ ማጋራት እንደሚፈልጉ መምረጥ እና ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። በማንኛውም ጊዜ አካባቢዎን ማጋራት ማቆም ይችላሉ።

ቅጽበታዊ አካባቢዎን ለሌሎች ያጋሩን ይመልከቱ።

ውሂብ እና ግላዊነት ማላበስ

Google ስለእኔ ምን ውሂብ ይሰበስባል?

የGoogle መተግበሪያዎችን እና ጣቢያዎችን ሲጠቀሙ እኛ እነሱን ለእርስዎ ለማቅረብ፣ ይበልጥ ለእርስዎ ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እና ለምን Google ውሂብ ይሰበስባል? ውስጥ እንደተገለጹት በሌሎች ምክንያቶች እኛ የሚያስፈልገንን መረጃ እንሰበስባለን።

በእርስዎ ቅንብሮች አማካኝነት እኛ የምንሰበስበውን ውሂብ እና ያ ውሂብ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል መገደብ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የእርስዎን የYouTube ታሪክ በGoogle መለያዎ ላይ እንድናስቀምጥ ካልፈለጉ የYouTube ታሪክን ማጥፋት ይችላሉ።Google ምን እንደሚያስቀምጥ እንዴት መወሰን እችላለሁ? የሚለውን ይመልከቱ

ውሂብ ምንድነው?

የግል መረጃዎ እንደ እርስዎ ስም ወይም የኢሜይል አድራሻ ያሉ በግል እርስዎን የሚለዩዎትን ነገሮች ያካትታል። እንዲሁም እንደ በGoogle መለያዎ ውስጥ ከእርስዎ ጋር የምናጎዳኘው መረጃ ያሉ በGoogle ከእርስዎ ጋር በተመጣጣኝ ሁኔታ ሊገናኝ የሚችል ሌላ ውሂብን ያካትታል።

የግል መረጃዎ ሁለት ዓይነት ነገሮችን ያካትታል፦

እርስዎ የሚሰጧቸው ወይም የሚፈጥሯቸው ነገሮች

Google መለያ ሲፈጥሩ እንደ እርስዎ ስም እና የይለፍ ቃል ያለ የግል መረጃ ይሰጡናል።

እንዲሁም እንደ የኢሜይል መልዕክቶች እና ፎቶዎች ያሉ እርስዎ የሚፈጥሩትን፣ የሚጭኑትን ወይም የሚቀበሉትን ይዘት ማስቀመጥ ይችላሉ።

በGoogle ላይ የሚያደርጓቸው ነገሮች

እንደ እርስዎ የሚፈልጓቸው ደንቦች እና የሚመለከቷቸው ቪዲዮዎች፣ የሚገናኟቸው ወይም ይዘትን የሚያጋሯቸው ሰዎች እና የተሻለ ተሞክሮ ለማቅረብ የእርስዎን የChrome የአሰሳ ታሪክ ያሉ ነገሮችን ሊያካትት የሚችል ስለእርስዎ ያለ እንቅስቃሴ በአገልግሎቶቻችን ውስጥ እንሰበስባለን።

የGoogle አገልግሎቶችን ለመድረስ ስለሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች፣ አሳሾች እና መሣሪያዎች መረጃ እንሰበስባለን፣ ይህም ባትሪዎ ዝቅተኛ ከሆነ እንደ ማያ ገጽዎን ማደብዘዝ ያሉ ባህሪያትን እንድናቀርብ ያግዘናል።

እንደ ተራ በተራ አቅጣጫዎች ያሉ ባህሪያትን ሲጠቀሙ ያሉበትን አካባቢ እናሰናዳለን። ለተጨማሪ መረጃ የአካባቢ ክፍልን ይመልከቱ።

Google ለምንድነው ውሂብ ይሰበስባል?

የእኛን አገልግሎቶች ለማቅረብ፣ ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ ለማድረግ እና ውሂብን በምንጠቀምባቸው መንገዶች ውስጥ እንደተገለጹት ሌሎች ምክንያቶች እኛ የሚያስፈልገንን መረጃ እንሰበስባለን።

ለምሳሌ፣ Google ካርታዎች እርስዎ የያሉበት ቦታ መረጃ (የእርስዎን ውሂብ) ከይፋዊ ውሂብ (ካርታዎች እና ስለሕዝባዊ ቦታዎች ያለ መረጃ) ጋር ስለሚያጣምር ትራፊክን እያስወገዱ ወደሚሄዱበት ቦታ እንዲደርሱ ሊያግዝዎ ይችላል።

ውሂብ የምንጠቀምባቸው መንገዶች

አገልግሎቶቻችንን ማቅረብ

ውጤቶችን ለመመለስ ሲባል እርስዎ የሚፈልጓቸውን ደንቦች እንደ ማሰናዳት ያሉ አገልግሎቶቻችንን ለማቅረብ ውሂብ እንጠቀማለን።

አገልግሎቶቻችንን ማቆየት እና ማሻሻል

ውሂብ አገልግሎቶቻችንን እንድንጠብቅ እና እንድናሻሽል ያግዘናል። ለምሳሌ፣ መቋረጥን መከታተል እንችላለን። እና የትኛዎቹ የፍለጋ ቃላት ፊደል በተደጋጋሚነት በስህተት እንደሚጻፉ መረዳት በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ የምንጠቀምባቸው የፊደል ማረሚያ ባህሪያትን እንድናሻሽል ያግዘናል።

አዲስ አገልግሎቶችን መገንባት

ውሂብ አዲስ አገልግሎቶችን እንድንገነባ ያግዘናል። ለምሳሌ፣ ሰዎች በመጀመሪያው የGoogle ፎቶዎች መተግበሪያ Picasa ውስጥ ፎቶዎቻቸውን እንዴት እንዳደራጁ መረዳት Google ፎቶዎችን እንድንነድፍ እና እንድንለቅቅ አግዞናል።

ይዘት እና ማስታወቂያዎችን ጨምሮ ግላዊነት የተላበሱ አገልግሎቶችን ማቅረብ

እኛ ግላዊነትን የተላበሰ ይዘት ለማቅረብ ውሂብን እንጠቀማለን፣ ለምሳሌ የወዷቸው የሚችሏቸው የቪዲዮዎች ምክሮች። በእርስዎ ቅንብሮች እና ዕድሜዎ ላይ የሚወሰን ሆኖ በእርስዎ ዝንባሌዎች ላይ ተመስርተን ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ልናሳየዎት እንችላለን።

አፈጻጸምን መለካት

እንዲሁም አፈፃፀምን ለመለካት እና የእኛ አገልግሎቶች እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ለመረዳት ውሂብን እንጠቀማለን

ከእርስዎ ጋር ግንኙነት መፍጠር

አጠራጣሪ እንቅስቃሴን ካገኘን ማሳወቂያ ለእርስዎ ለመላክ የኢሜይል አድራሻዎን ልንጠቀም እንችላለን

Googleን፣ ተጠቃሚዎቻችን እና ሕዝብን መጠበቅ

እንደ ማጭበርበርን መለየት እና መከላከል ያለ ሰዎችን በመስመር ላይ ደህንነታቸው የተጠበቀ ለማድረግ ውሂብን እንጠቀማለን

Google ነገሮችን ግላዊነት ለማላበስ እንዴት ውሂብ ይጠቀማል?

«ግላዊነት ማላበስ» የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ለእርስዎ ለማበጀት የምንሰበስበውን መረጃ ስለመጠቀም ነው፦

  • ሊወዷቸው የሚችሏቸው የቪዲዮዎች ምክሮች
  • የGoogle መተግበሪያዎችን እና ጣቢያዎችን እንዴት እንደሚጠቀሙ ላይ የተስተካከሉ የደህንነት ጠቃሚ ምክሮች (የደህንነት ፍተሻን ይመልከቱ)

ቅንብሩ ሲጠፋ ወይም ለተወሰኑ ዕድሜዎች ሲሆን ያሉ ሁኔታዎች በስተቀር ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ለማላበስም ውሂብ እንጠቀማለን።

Google እኔ የማያቸው ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ያላብሳል?

የምናሳያቸው ማስታወቂያዎች በተቻለ መጠን ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንሞክራለን። ነገር ግን ለተወሰኑ ዕድሜዎች ወይም ማስታወቂያ ግላዊነት ማላበስን ለሚያጠፉ ሰዎች ማስታወቂያዎችን ግላዊነት አናላብስም።

ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ሳናላብስ እንኳን ጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንችላለን። ለምሳሌ፣ የ«አዲስ ጫማዎች» የውጤቶችን ገጽን እየተመለከቱ ከሆነ ከስኒከር ኩባንያ ማስታወቂያ ሊያዩ ይችሉ ይሆናል። ማስታወቂያው እንደ የዕለቱ ሰዓት፣ አጠቃላይ አካባቢዎ እና እርስዎ የሚያዩት ገጽ ይዘት ባሉ አጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል።

እርስዎ ነዎት የሚቆጣጠሩት

Google በመለያዬ ላይ ምን እንደሚያስቀምጥ እንዴት መወሰን እችላለሁ?

እንደ ፎቶዎች ያሉ የGoogle አገልግሎትን ስለሚጠቀሙ የእርስዎን ፎቶዎች ምትኬ ማስቀመጥ እና ማስመር ያሉ ነገሮችን ይፈልጉ እንደሆነ መወሰን የሚያስችሉዎት ቅንብሮች አሉ።

በመላ የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ላይ የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊነት ለማላበስ የሚያግዙ ቅንብሮችም አሉ። ሁለቱ ቁልፎች የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ እና YouTube ታሪክ ናቸው።

እነዚህ መቆጣጠሪያዎች ሲበሩ፦

  • በGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ላይ ስላለው እንቅስቃሴዎ መረጃ በእርስዎ Google መለያ ላይ ይቀመጣል እና
  • የተቀመጠ መረጃ የGoogle ተሞክሮዎን ግላዊነት ለማላበስ ስራ ላይ ይውላል

የድር እና የመተግበሪያ እንቅስቃሴ

እንደ ፍለጋ እና ካርታዎች ባሉ የGoogle ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ላይ እንቅስቃሴዎን ያስቀምጣል እና እንደ አካባቢ ያለ ተጓዳኝ መረጃን ያካትታል። እንዲሁም ከጣቢያዎች፣ መተግበሪያዎች እና የGoogle አገልግሎቶችን ከሚጠቀሙ መሣሪያዎች የመጣ የሰመረ የChrome ታሪክ እና እንቅስቃሴን ያካትታል።

የእርስዎ እንቅስቃሴ በካርታዎች፣ በፍለጋ እና በሌሎች የGoogle አገልግሎቶች ውስጥ ፈጣን ፍለጋዎችን፣ የተሻሉ ምክሮችን እና ተጨማሪ ግላዊነት የተላበሱ ተሞክሮዎችን ለእርስዎ ለመስጠት ስራ ላይ ይውላል።

የYouTube ታሪክ

እርስዎ የሚመለከቷቸውን ቪዲዮዎች እና YouTubeን ሲጠቀሙ የሚፈልጓቸውን ነገሮች ያስቀምጣል።

የእርስዎ YouTube ታሪክ የYouTube ተሞክሮዎን እና እንደ የፍለጋ ውጤቶችዎ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎችን ግላዊነት ለማላበስ ስራ ላይ ይውላል።

የእኔን እንቅስቃሴ ውሂብ እንዴት መሰረዝ እችላለሁ?

በእርስዎ Google መለያ ውስጥ የተቀመጠውን ውሂብ መሰረዝ ይችላሉ። እስከመጨረሻው ለመሰረዝ የመረጡት ውሂብ ከስርዓቶቻችን ይወገዳል። ይህ ውሂብ ከአገልጋዮቻችን ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ወይም ከእርስዎ ጋር ሊጎዳኝ በማይችል መልክ ብቻ እንዲቆይ ለማድረግ ጥንቃቄ የተሞላበት ሂደት እንከተላለን።

እንደ እርስዎ የፈለጓቸው፣ ያነበቧቸው እና የተመለከቷቸው ነገሮች ያሉ በእርስዎ Google መለያ ውስጥ የተቀመጠውን እንቅስቃሴ ለመገምገም የእኔን እንቅስቃሴን ይጎብኙ። በተወሰነ የጊዜ ክልል ውስጥ የተወሰኑ የእንቅስቃሴ ክፍሎችን ወይም ሁሉንም እንቅስቃሴዎን መሰረዝ ይችላሉ።

እንዲሁም የእርስዎን እንቅስቃሴ በራስ-ሰር እንዲሰረዝ መምረጥ ይችላሉ።

ይዘቴን እንዴት ማውረድ እችላለሁ?

የእርስዎ ይዘት እንደ ኢሜይሎች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ ሰነዶች፣ ሉሆች፣ አስተያየቶች፣ እውቂያዎች እና የቀን መቁጠሪያ ክስተቶች ያሉ ነገሮችን ያካትታል።

የይዘትዎን ማህደር ለመፍጠር ውሂብዎን ያውርዱን ይጎብኙ - ለእሱ ምትኬ ለማስቀመጥ ወይም ሌላ አገልግሎት ለመሞከር ከፈለጉ ወደ ሌላ ኩባንያ ለመውሰድ።

ዘግቼ ስወጣ ምን መቆጣጠሪያዎች አሉኝ?

እርስዎ ዘግተው ሲወጡ እንኳ Googleን እንዴት እንደሚጠቀሙ እንዲመርጡ የሚያስችሉዎት መቆጣጠሪያዎች አሉዎት። ዘግተው ሲወጡ እነዚህን ቅንብሮች ለመቀየር g.co/privacytoolsን ይጎብኙ።

ፍለጋን ማበጀት

ለተጨማሪ ተዛማጅ ውጤቶች እና ምክሮች ከዚህ አሳሽ ሆኖ የእርስዎን Google ፍለጋዎች ይጠቀማል።

የYouTube ፍለጋ እና እይታ ታሪክ

YouTubeን ለእርስዎ ግላዊነት ለማላበስ እንደ እርስዎ የሚመለከቷቸው ቪዲዮዎች እና የሚፈልጓቸው ነገሮች ያሉ YouTube ላይ ያለዎትን እንቅስቃሴ ይጠቀማል።

እንዲሁም በአሳሽዎ ውስጥ አንዳንድ ወይም ሁሉንም ኩኪዎች ማገድ ይችላሉ፣ ነገር ግን ይህ በመላው ድር ላይ የተወሰኑ ባህሪያት መስራት እንዲያቆሙ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ፣ እርስዎ በመለያ መግባት ሲፈልጉ በርካታ ድር ጣቢያዎች የኩኪዎች መብራት ያስፈልጋቸዋል።

ምንም እንኳን ለተወሰኑ ዕድሜዎች ማስታወቂያዎችን ግላዊነት ባናላብስም ዘግተው የወጡ ተጠቃሚዎች ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለማየት ይፈልጉ እንደሆነ መምረጥ ይችላሉ።